Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

በእስራኤል እና ኢራን መካከል ያለው ግጭት የፈጠረው ተጽእኖ በአየር መንገዶች ላይ

በእስራኤል እና ኢራን መካከል ያለው ግጭት የፈጠረው ተጽእኖ በአየር መንገዶች ላይ

June 25, 2025
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

በእስራኤል እና ኢራን መካከል እየተካሄደ የሚገኘው ግጭት ተባብሶ በመቀጠሉ በርካታ አየር መንገዶች ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚያደርጉትን በረራዎች ለመሰረዝ ተገደዋል፡፡ ጦርነቱ አለምአቀፍ የአየር ጉዞን በማስተጓጎል በረራዎች እንዲሰረዙ እንዲሁም የመብረሪያ መስመሮችን እንዲቀይሩ እያደረገ ይገኛል፡፡

በመካከለኛው ምስራቅ የአየር ትራንስፖርት ማዕከል በሆነችው ኳታር የዶሃ አውሮፕላን ማረፊያ ኢራን በአሜሪካ ወታደራዊ ካምፕ ላይ ባካሄደችው ጥቃትን ተከትሎ ስራ አቁሞል፡፡ እንዲሁም የዱባይ አየር መንገድም ሲያደርጋቸው የነበሩትን በረራዎች ለጊዜው ማገዱን አስታውቋል፡፡

ኤር ኢንዲያ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚያደርጋቸውን በረራዎች በሙሉ እንደሚያቆም እና ወደ ሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ የሚያደርገውን በረራዎች እንደሚሰርዝ አስታውቋል። በተመሳሳይ የጃፓኑ ኤር ላይንስ ደግሞ ከቶኪዮ ወደ ዶሃ የሚያደርገውን በረራ መሰረዙን አሳውቋል፡፡

ከግጭቱ መባባስ ወዲህ በመካከለኛው ምስራቅ በየቀኑ ከ3,000 በላይ በረራዎች መሰረዛቸውን ፍላይት-ራዳር 24 ይፋ ያደረገው መረጃ ይጠቁማል፡፡ እስራኤል የመጀመሪያውን ጥቃት በኢራን ላይ ከፈጸመች በኋላ ከመደበኛ የተሳፋሪዎች በረራ በተጨማሪ የንግድ አውሮፕላኖች ከመብረር ተቆጥበዋል።በዚህም በቀን 1,400 የሚጠጉ በረራዎች በቱርክ ወይም በሳውዲ አረቢያ በኩል እንዲጓዙ ተገደዋል፡፡

ኩዌት፣ባህሬን፣ ሶሪያ፣ሊባኖስ፣እና ኢራን የአየር ክልላቸውን የዘጉ ሀገራት ሲሆኑ ኢራቅ እና ዮርዳኖስ በተደጋጋሚ የአየር ክልላቸውን ሲዘጉ እና ሲከፍቱ የነበሩ ሀገራት ናቸው፡፡ እስራኤል የአየር ክልሏን ለቅድመ ጥንቃቄ በሚል በቀዳሚነት የዘጋች ሀገር ናት፡፡ በርካታ አየር መንገዶችም የበረራ መስመራቸውን ለመቀየር የተገደዱ ሲሆን ከእነዛም መካከል ሉፍታንሳ፣ ኤር ፍራንስ፣ ብሪቲሽ ኤር ዌይስ፣ ኤር ኢንዲያ፣ ሲንጋፖር ኤርላይንስ እና የተለያዩ የአሜሪካ አየር መንገዶች ይገኙበታል፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ እስከ 820 በረራዎች መሰረዛቸውን የፍላይት አዌር (Flight Aware) መረጃ ያሳያል። አየር መንገዶቹ የግጭት ሰለባ በሆኑ ሀገራት የሚያደርጉትን በረራዎች ላለመሰረዝ አማራጭ መንገዶች እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡ አውሮፕላኖቹ የሚያደርጉት ረጅም በረራዎች በርካታ ነዳጅ እንዲጠቀሙ ያደርጋቸዋል። ይህ ደግሞ የነዳጅ ዋጋ እየጨመረ ባለበት ወቅት ለአየር መንገዶቹ ተጨማሪ ወጪ ያስከትላል።

የመብረሪያ መንገዳቸውን የቀየሩ አየር መንገዶች አዲስ የአየር ክልሎችን በመጠቀማቸው ተጨማሪ ክፍያዎችን እንዲከፍሉ ይገደዳሉ፡፡ የአየር መንገዶቹ የሚያጋጥማቸውን ከፍተኛ ወጪ ለመሸፈን የቲኬት ዋጋዎችን ከፍ ሊያደርጉ እንደሚችሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ሀሳባቸውን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ግጭት የአየር መንገዶችን በረራዎች አቅጣጫ እንዲቀይሩ በማስገደድ ለአደጋ ተጋላጭ የሚሆኑበትን እድል እያባባሱ ይገኛል። ቀድሞውንም በሩሲያ-ዩክሬን ግጭት ምክንያት ወደ መካከለኛው ምስራቅ የተዘዋወሩትን በረራዎች አሁን ደግሞ በእስራኤል እና ኢራን ጦርነት ምክንያት ወደ ሌሎች አየር ማረፊያዎች ፊታቸውን ማዞራቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ጫናን በአየር መንገዶቹ ላይ እየፈጠሩ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

በ-ሀሴት ሀይሉ

Source: @NBCEthiopia
Via: NBCEthiopia
Tags: #ISRAEAL GAZAEthiopiaFacebookiranIsraelMeta
ShareTweetShare
Previous Post

ማእከላዊ ጎንደር ዞን አዘዞ አካባቢ የሚገነባው መገጭ መስኖ ግድብ ፕሮጀክት

Next Post

አውሮፓ ህብረት በኔቶ ማዕቀፍ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
5
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
6
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
13
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
50
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
34
Next Post
አውሮፓ ህብረት በኔቶ ማዕቀፍ

አውሮፓ ህብረት በኔቶ ማዕቀፍ

ዓለም አቀፍ የጤና ኢኖቬሽን እና ጥራት ጉባኤ

ዓለም አቀፍ የጤና ኢኖቬሽን እና ጥራት ጉባኤ

ኬፓ አሪዛባላጋ ወደ አርሰናል የሚያደርገውን ዝውውር በሳምንቱ መጨረሻ ያጠናቅቃል ተባለ

ኬፓ አሪዛባላጋ ወደ አርሰናል የሚያደርገውን ዝውውር በሳምንቱ መጨረሻ ያጠናቅቃል ተባለ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?