፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል፡፡
በዚህም የማለፊያ ነጥብ 50 በመቶ እንዲሆን የትምትርት ቢሮ አጠቃላይ ትምህርት ካውንስል መወሰኑ ተገልጿል።
ለአካል ጉዳተኛ እና የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች የማለፊያ ነጥቡ 45 በመቶ እና ከዚያ በላይ ሆኖ ተወስኗል። 97 ነጥብ 3 የ2017 የከተማው ከፍተኛ ነጥብ ሆኖ ተመዝግቧል።
በከተማ አስተዳደሩ በ2017 ዓ.ም 70 ሺህ 525 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ሲሆን 88 ነጥብ 8 በመቶ ከ50 በመቶ በላይ ማምጣታቸው ተገልጿል።
ስምንተኛ ክፍል ካስፈተኑ 656 ትምህርት ቤቶች መካከል 276 ትምህርት ቤቶች መቶ በመቶ ማሳለፋቸው ተመላክቷል። በከተማ ደረጃ 20 ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች መካከለወ 13 ከአዳሪ ትምህርት ቤት ናቸው።
በከተማ አስተዳደሩ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በየዓመቱ መሻሻል እያሳየ መምጣቱም ተገልጿል፡፡
በመንግስት እና በግል ትምህርት ቤቶት መካከል የነበረውን ከግማሽ በላይ የውጤት ልዩነትም ወደ ስድት በመቶ ማጥበብ ተችሏል።
የ2017 የስደስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት በቀጣይ ሳምንት ይፋ እንሚሆን ነው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዘላለም ሙላቱ የገለጹት።
በ-የአብስራ ብርሀኑ












