ዲሚትሪ ፓዬ የቀድሞ ባለቤቱ ላይ ባደረሰው ዘርፈ ብዙ አካላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጥቃት ተጠያቂ መደረጉ ተሰማ።
የቀድሞ የዌስትሃም አስደናቂ አማካኝ ዲሚትሪ ፓዬ በብራዚል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶበታል።
የ38 አመቱ ፓዬ ከቀናት በፊት ኮንትራቱ እስኪያበቃ በብራዚሉ ቫስኮ ዳጋማ ክለብ በመጫወት ላይ ይገኝ ነበር።
የተጫዋቹ የቀድሞ ባለቤቱ ላይ ላሪዛ ፌራሪ በትዳር አብረው በቆዩባቸው አመታት የፈጸመባትን ጥቃት አስመልክቶ ክስ መስርታለች።
ዲሚትሪ ፓዬ እና ጠበቃዋ ላሪዛ ፍቺ የፈጸሙት ተጫዋቹ ከወራት በፊት ሲሆን፣ 4 ልጆችንም አፍርተዋል።
ላሪዛ በሰጠችው ቃል የቀድሞ ባለቤቷ በጸያፍ ቃላት አዕምሮዋን ከመንካት አንስቶ አካላዊ ጥቃት ያደርስባት እንደነበር አንስታለች።
“ከቅርብ አመታት ወዲህ ከርሱ ጋር ያሳለፍኩት ህይወት የስቃይ ነበር” የምትለው ላሪዛ ‘’የመጸዳጃ ውሃ እንድጣጣ፣ከዚያም አልፎ የውሃ ሽንት እንድጠጣ አድርጎኛል” በማለት ተናግራለች።
በተጨማሪም ክብሬን በሚነካ አስነዋሪ ድርጊት በሚፈጸም ፊልም እንድተውን ያስገድደኝ ነበር ስትል ክሷን አሰምታለች።
የከሳሿን ቃል የተቀበለው የሪዮ ዲ ጄኔሮ ፖሊስ በቀድሞው ተጫዋች ላይ ክስ መመስረቱን አስታውቋል።
በዌስትሃም ቆይታው በድንቅ የቅጣት ምት ጎሎቹ የሚታወሰው ፓዬ በቀድሞ ባለቤቱ ላይ የፈጸመው ድርጊት እያነጋገረ ይገኛል።
ተጫዋቹን በቅርበት የሚያውቁ ሰዎች እንደሚሉት ፓዬ ከቅርብ አመታት ወዲህ የአዕምሮ መረበሽ እየታየበት እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












