
በአሜሪካ አስተናጋጅነት እየተከሄደ የሚገኘው የመጀመሪያው የአለም ዋንጫ በተመልካች ድርቅ መመታቱ አሳሳቢ ሆኗል። 32 ክለቦች ተሳታፊ በሆኑበት የአለም ዋንጫው በመጀመሪያ ዙር የምድብ ጨዋታዎች ስታዲየሞች ከ50 በመቶ በላይ መቀመጫቸው ባዶ ነበር ተብሏል።
ኢንተር ሚያሚ ከ ግብጹ አል ሂላል ካደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ አንስቶ ትላንት ማታ እስከተደረጉ ጨዋታዎች ድረስ 400ሺ ወንበሮች ክፍት እንደነበሩ ተነግሯል።
እስካሁን ከታዩ ጨዋታዎች 60ሺ ደጋፊዎች የታደሙበት ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ከ አል ሂላል ያደረጉት ጨዋታ ሲሆን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተመልካች የታየበት ነው ተብሏል።
እጅግ ዝቅተኛ የተመልካች ቁጥር የታየበት ጨዋታ ማሜሎ ሰን ዳውንስ ከ ኡልሳን ያደረጉት 3ሺ ደጋፊዎች የታደሙበት ግጥሚያ ነበር።
በውድድሩ መስራቾች በኩል ከስታዲየም ገቢ ለማግኘት ተይዞ የነበረው ዕቅድ እስካሁን ባለው የተሳካ አይመስልም። የአውሮፓ ክለቦች እርስበርስ በሚገናኙበት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች የተሻለ የተመልካች ቁጥር ሊመዘገብ ይችላል የሚል ግምት ተወስዷል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












