:::::::::::::::::::::::::::::::::
ደቡብ ኮሪያዊው ሶን በአል ሂላል፣አል ናስር እና አል ቃዲሽ ክለቦች በዝውውር ገበያው ቀዳሚው ኢላማ መሆኑን ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል።
ሶን ከሰሜን ለንደኑ ክለብ ያለው ኮንትራት በቀጣይ አመት የሚጠናቀቅ ሲሆን ቶተንሃም ተጫዋቹን በአጥጋቢ ሂሳብ ለመሸጥ ያለው የመጨረሻው ጊዜ ነው ተብሏል።
ቶተንሃም የ32 አመቱ ተጫዋች በክለቡ ለማቆየት እስካሁን የተሻሻለ ውል አለማቅረቡ ታውቋል።
ለ 10 አመት በቶተንሃም የቆየው ሶን በዘንድሮው አመት ብቃቱ ቀንሶ የውድድር አመቱ በርካታ ጨዋታዎች ከተጠባባቂ ወንበር ተንስቶ ሲጫወት ታይቷል።
የሳዑዲዎቹ ክለቦች እያንዳዳቸው ለተጫዋቹ እስከ 40 ሚሊዮን ፓውንድ ለመክፈል ዝግጁ ናቸው ተብሏል።
በተጫዋቹ በኩል እስከሁን የተሰጠ አስተያየት ባይኖርም፣ቶተንሃም ጥያቄው ገፍቶ ከመጣ ተጫዋቹን መሸጡ አይቀርም እየተባለ ነው።
ሶን ሂዮንግ ሚን በ10 አመት የሰሜን ለንደን ቆይታው 169 ግቦችን ለቶተንሃም አስቆጥሯል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












