:::::::::::::::::::::::::::::::::::::
የቀድሞው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሳውዝጌት በይሮ 2024 ፍጻሜ በስፔን ተሸንፈው ሃላፊነታቸውን ክለቀቁ ወዲህ ዳግም ወደ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ሊመለሱ እንደሚችል እየተዘገበ ይገኛል።
የፖላንድ መገናኛ ብዙሃን ባወጡት ዘገባ ብሔራዊ ቡድኑን ለመረከብ ፍላጎት ካሳዩና የሃገሪቱን እግር ኳስ ፌዴሽን ካናገሩ ሰዎች መካከል ሳውዝጌት እንደሚገኙበት አመላክተዋል።
ከቀናት በፊት በፖላንድ ብሔራዊ ቡድን በተነሳ ውዝግብ መነሻነት አሰልጣኝ ሚሌል ፕሮቢርዝ በገዛ ፈቃዳቸው ሃላፊነታቸውን እንደለቀቁ ይታወሳል።
የ54 አመቱ ሳውዝጌት በሶስቱ አናብስት የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የ8 አመት ቆይታቸው በዋንጫ አሸናፊነት ባይታጀብም፣ቡድኑን ውጤታማ በማድረግ እና ለፍጻሜ እንዲደርስ በማስቻል ተደናቂነት አግኝተዋል።
በብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ከፍተኛ ደመወዝ ተከፋይ የነበሩ ሲሆን፣የፖላንድ ብሔራዊ ቡድን ተመሳሳዩን መክፈል ባይችልም ሃላፊነቱን ለመረከብ ይፈልጋሉ ተብሏል።
ፖላንድ በ2026ቱ የአለም ዋንጫ ተካፋይ ለመሆን በወሳኝ የማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ ትገኛለች።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












