የእንግሊዝ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባወጣው መግለጫ በ20 ክለቦች መካከል የሚደረገው እና 380 ጨዋታዎች የሚከናወኑበት መርሃ ግብር በነገው ማለዳው ይታወቃል ተብሏል።
የ2025-26 የውድድር አመት የመክፈቻ ጨዋታ በአውሮፓውያን ነሐሴ 16 በዕለተ ቅዳሜ የሚደረግ ሲሆን የመዝጊያ ጨዋታዎች ደግሞ ግንቦት 24 -2026 እንደሚሆን ታውቋል።
ሊጀመር 83 ቀናት በቀሩት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በተጠናቀቀው አመት ሻምፒዮን የሆነው ሊቨርፑል ራሱን በማጠናከር ላይ ሲሆን፣ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በተከታታይ የሊጉ አሸናፊ ለመሆን ይዘው የሚቀርቡት ቡድን ይጠበቃል።
እስካሁን ባለው 4 ተጫዋቾችን ያስፈረመው ሲቲ ከደካማ የውድድር አመት በኋላ ወደ ሊግ አሸነፊነቱ ይመለሳል የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ሲሆን በተከታታይ ሶስት አመት ሁለተኛ ስፍራን የሙጥኝ ያለው አርሰናልም በቀጣይ የውድድር አመት እየተጠበቀ ይገኛል።
ፕሪምየር ሊጉን ከ8 አመት ቆይታ በኋላ የተቀላቀለው ሰንደርላንድ ከከተማ ተቀናቃኙ ኒውካስትል የሚገናኝ በመሆኑ የሊጉ ድምቀት ይሆናል ተብሏል።
የ33 ሳምንት እና የ 5 የሳምንት አጋማሽ ጨዋታዎች የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ነገ ጠዋት ይከናወናል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












