።፡፡።፡።።፡፡።፡።።፡፡።፡።።፡፡።፡።
ሩሲያ እስራኤል በኢራን የምትፈጽመው ጥቃት ህገ ወጥ ነው ስትል አወገዘች፡፡
እስራኤል በኢራን ላይ የምትፈጽመው ተደጋጋሚ ጥቃት ህግ ወጥ ነው በሚል ያወገዘችው ሞስኮ የቴህራን የኑክሌር ጉዳይ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መታየት ያለበት ነው በሚል አሳስባለች።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባጋራው መግለጫው ላይ ኢራን ኑክሌርን አሳልፎ ባለመስጠት እና ያለአግባብ አለማባዛት ስምምነት
(NPT) ተገዥ ለመሆን ቁርጠኝነቷን በግልጽ አስቀምጧል፡፡
የቴህራንን መግለጫ ግምት ውስጥ አስገብታ ነው ሞስኮ በመርህ መተዳደር አለብን ያለችው፡፡
ኢራን ከአሜሪካ ጋር በጉዳዩ ላይ ለመነጋገርም ዝግጁ መሆኗን መግለጫው አብራርቷል።
ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ሀይል ድርጅት እስራኤል በኢራን የኑክሌር ማብላያዎች ላይ ላደረሰችው ጉዳት ግልጽ ትንተና ሞስኮ እየተጠባበቀች ስለመሆኗም ተወስቷል።
የአሜሪካ ሀይሎች በጦርነቱ ላይ ያላቸውን አቋም ከዕለት ወደ ዕለት እየለወጡ በመጡበት ሰዓት ሞስኮ የቴህራንን ፍላጎት ወደ ዓለም አቀፉ መድረክ ይዛ ብቅ እያለች ነው በሚል በኢራን ደጋፊዎች ተስፋ ተጥሎባታል።
አልጀዚራ እንዳስነበበው።
በ-ቢኒያም ካሴ












