ኢራን ውስጥ የተወለደችው ዞሊያ አለሚ እና ቤተሰቧ በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ ወደ ኒውዚላንድ አመሩ። እዚያም እንደ ብቁ ሐኪም ለመስራት የሚያስፈልገውን የሕክምና የመጀመሪያ ዲግሪ እና የቀዶ ጥገና ዲግሪ ትምህርት ማግኘት አልቻለችም። ነገር ግን ይህ ህልሟን ከመፈጸም ወደ ሆላ እንዲያስቀራት አልፈቀደችም።
በ90ዎቹ አጋማሽ ላይ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም በመዘዋወር ዶክተሮች ያለ ተጨማሪ ምርመራ እንዲለማመዱ የሚያስችል የህግ ክፍተት በመጠቀም የተጭበረበሩ ወረቀቶችን ማግኘት ቻለች።
በእነዚህ በተጭበረበሩ ወረቀቶችም በመጠቀም ለ20 ዓመታት ያህል በመላው ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የአእምሮ
ህክምናን ሠጠች።
አለሚ ለታካሚ ደህንነት እንዲሁም ለስነልቦናቸው ምንም ዓይነት ጥንቃቄ እንደሌላት የተገለፀ ሲሆን ለ20 ዓመታት ያህል የኤን ኤች ኤስ ሳይካትሪስት ሆና ለመቀጠር ፎርጅድ የኒውዚላንድ የሕክምና መመዘኛዎችንም ተጠቅማለች።
አለሚ በዩናይትድ ኪንግደም ብሔራዊ የጤና አገልግሎት ከ20 ዓመታት በላይ ስትሰራ ከ1.2 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ገቢ እንዳገኘች እና የታካሚዎቿን ህይወት አደጋ ላይ ጥላለች ሲል አቃቤ ህግ ተናግሮ በአለሚ ላይም በማጭበርበር ወንጀል ክስ መመስረቱን ገልጿል።
የዩናይትድ ኪንግደም አጠቃላይ የህክምና ምክር ቤት በ1990ዎቹ የተሰጡ ወደ 3,000 የሚጠጉ የባህር ማዶ ዶክተሮች ፍቃድ ላይ ትልቅ ግምገማ መጀመሩን ገልጿል።
በ – ሔርሜላ ተመስገን












