ቀን 9 ሰዓት ላይ የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊው ሲዳማ ቡና ከድሬዳዋ ከተማ ይገናኛሉ።
ድሬዳዋ ከተማ 39 ነጥብ በመያዝ 13ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በሂሳባዊ ስሌት አሁንም በፕሪምየር ሊግ መቆየቱን አላረጋገጠም።
በወራጅ ቀጠናው ካሉ ቡድኖች ያለው የነጥብ ርቀት 1 ብቻ በመሆኑ በሊጉ ለመቆየት በቀሪ ጨዋታዎች የማሸነፍ ግዴታ ውስጥ ገብተዋል።
በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የዋንጫ አሸናፊ የሆነው ሲዳማ፣በደረጃ ሰንጠረዥ 6ኛ ላይ ይገኛል።
ሲዳማ ቡና በጥሩ መነቃቃት ላይ ሲሆን የዛሬውን ጨዋታ በድል ከተወጣ ነጥቡን 49 በማድረስ 3ኛ ደረጃን ከባህር ዳር መውሰድ ያስችለዋል።
ምሽት 12 ሰዓት በኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ የተሸነፈው ወላይታ ድቻ ባህርዳር ከተማን የሚገጥም ይሆናል።
በደረጃ ሰንጠረዥ 8ኛ ላይ የሚገኘው ድቻ ካደርጋቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ብቻ ነው።
የምሽቱ ጨዋታ ደረጃውን የሚያሻሽልበት ብቻ ሳይሆን ከተከታዮቹ የሚጠብቅበት ጭምር በመሆኑ ጨዋታውን ተጠባቂ ያደርገዋል።
ባህር ዳር ከተማ ካደረጋቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች አንዱንም ያልቻለ ሲሆን ደካማ አቋም ላይ ይገኛል።
የሚገኝበትን 3ኛ ደረጃ ለማስጠበቅ እና 2ኛ ላይ ከሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ የምሽቱን ጨዋታ በድል መወጣት ይኖርበታል።
ጨዋታዎቹ በተያዘላቸው ሰዓት በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይከናወናሉ።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












