በ- አልፈሪድ ነስሮ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአትሌት ገለቴ ቡርቃ የደረሰን በደል አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፣ የአትሌቶች ማህበር ፕሬዚዳንት አትሌት የማነ ፀጋይ አትሌቶችን ለግላዊ ጥቅም ማሳደግ የተለመደ እና እንደ ገቢ ምንጭ የሚወሰድ ተግባር ሆኗል ብለዋል።
በአትሌቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት እና እንግልት ከክለብ እንደሚጀመር፣ ወደ መገናኛ ብዙሃን ወጥተው በደላቸውን እንዳይናገሩ ማስፈራሪያ እንደሚደርስባቸው ገልፀዋል። ጥቃቱ በሴት አትሌቶች ብቻ ሳይሆን በወንድ አትሌቶችም እየተፈፀመ የሚገኝ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
በሴት አትሌቶች ላይ ፆታዊ ጥቃት በአሰልጣኞች እና ማናጀሮችም እየደረሰ የሚገኝ፣ ለዓመታት ምላሽ ሳይሰጠው ተሸፍኖ የከረመ ጉዳይ መሆኑ ተመላክቷል።

Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBC Ethiopia