በ-ሰላማዊት ወንድወሰን

እስራኤል በጋዛ ከ90 በመቶ በላይ ትምህርት ቤቶችን ማውደሟን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት አመላከተ፡
በተባበሩት መንግስታት የአለምአቀፍ ገለልተኛ የምርመራ ኮሚሽን ይዞት በወጣዉ ሪፖርት፣ እስራኤል በጋዛ የትምህርት፣ የሃይማኖት እና የባህል ስፍራዎች ላይ እየፈጸመች ያለችው ጥቃት የጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጥፋት ነው ሲል ከሷል፡፡
ኮሚሽኑ እስራኤል የጋዛን ነዋሪዎች ማንነትን የሚገልጹ እንደ ባህል፣የእምነት እና ታሪካዊ ስፍራዎች እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን በማውደም እያደረሰችው ያለው አስከፊ ተግባር ተጠያቂ ያደርጋታል ብሏል፡፡
ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ባወጣዉ ሪፖርት እስራኤል በጋዛ የሴቶችን የጤና መጠበቂያ ተቋማት በማውደም ስልታዊ በሆነ መንገድ የዘር ማጥፋት ድርጊቶችን ፈጽማለች ሲል መክሰሱ ይታወሳል፡፡
ክሱን ተከትሎ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ሪፖርቶቹ አድሎአዊ እና ፀረ ሴማዊ ናቸው ሲሉ ሀገራቸው ከኮሚሺኑ እራሷን እንድታገል አድርገዋል፡፡
የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የነበሩት የቀድሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ናቪ ፒሌይ፣ እስራኤል በጋዛ ትምህርት ተቋማት፤ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ስፍራዎች ለይ የፈጠመቻቸው ጥቃቶች አለም አቀፍ ህጎች መጣሷን ያገጋገጡ መሆናቸውን በሪፖርቱ ተመልክተናል ብለዋል፡፡












