።።።።።።።።።።።።።።።
“በሁለተኛ አመት ዋንጫ የማንኘት ታሪክ አለኝ” – አንጅ ፖስትኮግሉ
የሰሜን ለንደኑ ቶተንሃም ሆትስፐር ከ17 አመት የዋንጫ ረሃብ በኋላ ትላንት ምሽት መጥፎ ታሪኩን የቀየረበት፣ደካማ የውድድር አመቱን ያካካሰበትን የዩሮፓ ሊግ ዋንጫ አሳክቷል።
ሁለት የእንግሊዝ ቡድኖችን፣በሊጋቸው ከወራጅ ቀጠና አፋፍ ላይ የተቀመጡ ቡድኖችን ያገናኘው ጨዋታ፣በቀያይ ሰይጣኖቹ የጨዋታ ቁጥጥር የበላይነት ቢወሰድም ስፐርስ ዋንጫውን የራሱ አድርጓል።
አሰልጣኝ ፖስትኮግሉ በውድድር አመቱ መጀመሪያ “በአንድ ክለብ በሚኖረኝ የሁለተኛ አመት ቆይታ ዋንጫ የመግኘት ታሪክ አለኝ” ሲሉ የሰጡት አስተያየት መሳለቂያ ሲያደርጋቸው ቆይቷል።
በጊዜው አሰልጣኙ ላይ ስላቅ የተሞሉ አስተያየቶች የተሰጡት የሚያሰለጥኑት ክለብ ቶተንሃም ከዋንጫ የተኳረፈ፣እንደ ገደ ቢስ ቡድን የሚታይ ስለነበር ነው ትላንት ምሽት ታሪክ ተለውጦ ቶተንሃም ሆትስፐር ባለድል መሆን ችሏል።
አሰልጣኝ ፖስትኮግሉም ቃላቸውን በተግባር አሳይተው፣ በቡድኑ ደካማ የሊግ የውድድር አመት ልባቸው ያዘነ ደጋፊዎችን ክሰዋቸዋል።
የፍጻሜ ጨዋታው የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ቲኬትን ለመቁረጥ የሚያስችል በመሆኑ እጥፍ ድርብ ደስታ ሆኖላቸዋል።
ስፐርስ በውድድር አመቱ መጨረሻ አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም በመማተር ላይ ሲሆን ከአያክስ አምስተርዳሙ አሰልጣኝ ፍራንሲስኮ ፋሪዮሊ ጋር ንግግር ጀምረዋል።
ፖስትኮግሉ ትላንት ምሽት ባሳኩት ዋንጫ መነሻነት በጥሩ መንፈስ ከክለቡ የሚለያዩበትን መደላድል ፈጥረዋል።
ስፐርስ ለአሰልጣኙ ተጨማሪ ዕድል ይሰጥ ይሆን ?
በ- አልፈሪድ ነስሮ












