ባርሴሎና የላሊጋ አሸናፊነቱን ካወጀበት የካታላን ደርቢ ጨዋታ አስቀድሞ በኤስፓኞል ስታዲየም አቅራቢያ የመኪና አደጋ ደርሶ በ13 ሰዎች መጠነኛ ጉዳት መድረሱን የከተማዋ ፖሊስ አስታውቋል።
አደጋው የደረሰው የኤስፓኞል ደጋፊዎች የክለቡን አሰልጣኝ ተመልክተው ድጋፍ ለመስጠት በተሰባሰቡበት ወቅት ነበር።
እንደ ፖሊስ ሪፖርት አደጋውን ያደረሰው “ስርዓት አልበኛ ጽንፈኛ ደጋፊ” መሆኑን እና ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ ሲያስከረክር እንደነበር ተገልጿል። ደጋፊው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ነውም ተብሏል።
አደጋ የደረሰባቸው ደጋፊዎች በአፋጣኝ ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን በስታዲየሙ ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱ ተመላክቷል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












