፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በአዲስ አበባ ዛሬ የሚጀመረው የምስራቅ አፍሪካ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ETEX 2025 ለሦስት ቀናት ይቆያል።
ከ10 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች እንደሚታደሙበት የሚጠበቀው ይህ ኤክስፖ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያተረፉ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት ነው።
በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በዛሬው ዕለት በይፋ የሚከፈተው ኤክስፖው ከመቶ በላይ የአገር ውስጥና የውጭ የቴክኖሎጂ አቅራቢዎች የቅርብ ጊዜ ምርቶቻቸውንና አገልግሎቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበት መድረክ ነው።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርና የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሳይበር ደህንነት ተቋም ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ይህ ኤክስፖ የተለያዩ የፓናል ውይይቶችንና የቴክኖሎጂ ውድድሮችንም ያካትታል።
በተለይም በሳይበር ደህንነት፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በስማርት ሲቲ እና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ውይይቶች እንዲሁም የሮቦቲክስና ሌሎች የቴክኖሎጂ ውድድሮች በኤክስፖው እንደሚካሄዱ ይጠበቃል።












