::::::::::::::::::::::::
ቪክቶሪያ ሊ ከቻይና ቤጂንግ የተገኘች የንቅሳት ባለሞያ ነች።ልክ እንደ ፎቶግራፍ ጥርት ያሉ ንቅሳቶችን በሰዎች ሰውነት ላይ ትሰራለች ንቅሳት በጀመረችባቸው ጊዜያት የተለመደውን የንቅሳት ዓይነት ማለትም ጥቁር እና ነጭ ቀለሞችን ብቻ በመጠቀም ትሰራ ነበር ከጊዜያት በኋላ ያልተለመዱ የቀለም ዓይነቶችን በመጠቀም የተለያዩ ንቀሳቶችን በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡

ሊ እንድምትገልጽው ከ4 ዓመቷ ጀምሮ የስነ-ጥበብ ስራዎች እንደሚያስደስታት እና በዛም ውስጥ እንደነበረች ገልጻለች ወደ ንቅሳት ሞያም የገባችው የአያትዋን ፎቶ ለመነቀስ ፈልጋ በፈለገችው መልኩ የሚሰራላት ባለማግኘቷ የፈጠረባት ስሜት ወደ እዚህ የንቅሳት ሞያ እንድትገባ አድርጓታል፡፡

ሊ እንድ እ.ኤ.አ ከ2014 ጀምሮ የንቅሳት ባለሞያ መሆኗን የዘገበው ኦዲቲ ሲንትራል ነው፡፡
በ-ሔርሜላ ተመስገን












