::::::::::::::::::::::
የባየርን ሊቨርኩሰኑ አሰልጣኝ ከቀናት በፊት ከጀርመኑ ክለብ በክረምት እንደሚለያይ ማስታወቁ ይታወሳል።
አሁን ላይ ይፋ እንደተደረገው አሎንሶ በተጫዋችነት ያሳለፈበትን ሪያል ማድሪድ በአሰልጣኝነት በክረምት ለመረከብ መስማማቱ ተነግሯል።
እስከ አውሮፓውያኑ 2028 በሎስብላንኮዎቹ ቤት የሚያቆየውን ውል እንደሚፈርምም ታውቋል።
አሰልጣኝ ካርሎ አንቼሎቲ በውድድር አመቱ መጨረሻ ጨዋታ ላይ ሽኝት የሚደረግላቸው ሲሆን በቀጣይ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነትን እንደሚረከቡ ይጠበቃል።
ዥቪ አሎንሶ ከውድድር አመቱ የመጨረሻ ጨዋታ በኋላ ቡድኑን ተረክቦ ለአለም ክለቦች ሻምፒዮና የሚያዘጋጅ ይሆናል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












