::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ከማኑኤል ፔሌግሪኒ ጋር ለፍጻሜ በመድረሳቸው መደሰታቸውን ገለጹ።
የቼልሲው አሰልጣኝ በአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ ዴር ጉደንን በድምር ውጤት 5-1 አሽንፈው በፍጻሜው ከስፔኑ ሪያል ቤቲስ ጋር ተገናኝተዋል።
ማሬስካ ከሪያል ቤቲሱ አንጋፋ አሰልጣኝ ማኑኤል ፔሌግሪኒ ጋር የቀደመ የስራ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን ለሁለት አመት በተጫዋችነት፣ በሌላ ሁለት አመት ደግሞ ረዳት አሰልጣኝ በመሆን አብረው ለመስራት ችለዋል።

ፔሌግሪኒ በማላጋ አሰልጣኝ በነበሩበት ዘመን ከነበሯቸው ተጫዋቾች ውስጥ ማሬስካ አንዱ ነበሩ፣ በእንግሊዝ ዌስትሃም ዩናይትድን በሚያሰለጥኑበት ጊዜም ከአሰልጣኝ ቡድን ስብስባቸው ውስጥ ማሬስካን አካተው ነበር።
የሰማያዊዎቹ አሰልጣኝ ማሬስካ “የሙያ አባቴን በፍጻሜው ለመግጠም በመቻሌ ደስተኛ ሆኛለሁ” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
አያይዘውም “ ማኑኤል ለተጫዋቾች የሚሰጠውን ስልጠና በሚገባ አውቃልሁ፣ቀረቤታው ግልጽነትን መሰረት ያደረገ ቅን ሰው ነው’’ ሲሉ ገልጸዋቸዋል።
በቼልሲ እና ሪያል ቤቲስ መካከል የሚደረገው የኮንፈረንስ ሊግ ፍጻሜ በአውሮፓውያን ግንቦት 28 በፖላንድ ይደረጋል። የዋንጫው አሸናፊ የሚሆነው ክለብ በቀጥታ የይሮፓ ሊግ ተሳታፊነትን ያረጋግጣል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












