፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የኒው ዮርክ ፖሊሲ የፍልስጤም ደጋፊዎች ያላቸውን በርካታ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር አዋለ፡፡
የፍልስጤም ደጋፊዎች በትራምፕ አስተዳደር የተጣለውን እገዳ በመቃወም ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በቤተ-መጽሀፍት በግዳጅ ገብተዋል። የዩኒቨርስቲው አስተዳደር ክሌር ሺፕማን በሠጡት መግለጫ ተቃዋሚወች ወደ ቤተ-መጽሐፍቱ ሲገቡ የፊት መሸፈኛ ጭምብሎችን እንደተጠቀሙ እና የዩኒቨርሲቲው የፀጥታ አካላት መቁሠላቸውን ገልፀዋል።

የፍልስጤም ደጋፊወች “ነፃ ፍልስጤም” በሚል መፈክሮች ታግዘው ተቃውሞውን አካሔደዋል። የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ኘሬዝዳንት እንደገለፁት የትምህርት እንቅስቃሴወችን ለማደናቀፍ የሚደረጉ ተግባሮች በምንም ዓይነት መልኩ ተቀባይነት የላቸውም።
እንደሚታወቀው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የሚሠጠውን የ 400 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ እንደሚያስቀር ገልፀው ነበር። ዘገባው የBBC ነው፡፡
በ-ሔርሜላ ተመስገን












