እንቁላል እና መዘዙ
። ። ። ። ። ። ። ።።
የስዊድን ነዋሪ የሆነችው የ24 ዓመት እናት በልጇ ጭንቅላት ላይ የሰበረችው እንቁላል በህግ አስቀጣት፡፡
ይህቺ እናት በሴት ልጇ ግንባር ላይ እንቁላል በመስበር ለተመልካቾች የመዝናኛ ምስል በቲክቶክ ታጋራለች። ይህም ምስል ከ100,000 በላይ ተመልካቾች ቢኖሩትም፤ በምስሉ ላይ ህፃኗ ጉዳት እንዳለው ለእናቷ እየገለፀችላት ያሳያል ይህ የህፃኗ መልዕክት ያስቆጣቸው ተመልካቾችም ለፖሊስ ሪፖርት አድርገዋል። የስዊድን ፖሊስም ምርመራ በማካሄድ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስዶታል፡፡
የ24 ዓመቷ እናት፣ ጉዳዩ ቀልድ ብቻ እንደነበር እና ሁሉም ሰው በወቅቱ በቲክቶክ ላይ የሚያደርገው ልማድ መሆኑን ብትገልፅም ከጥፋተኝነት ግን ሊያድናት አልቻለም። ጉዳዩን የያዘው የስዊድን ፍርድ ቤት “የገዛ ልጇን ያለፍላጎቷ በማዋከብ” በሚል ለልጇ የሚከፈል 2,070 የአሜሪካ ዶላር ቀጥቷታል፡፡ ዘገባው የoddity central
በ- ሔርሜላ ተመስገን












