ኤሲ ሚላን ከቦሎኛ በሳንሲሮ ምሽት 3፡45 ሲል ይገናኛሉ።
ሚላን በሴሪ ኤ የደረጃ ሰንጠረዥ 57 ነጥቦችን ሰብስቦ 9ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ቦሎኛ በአንፃሩ በ5 ነጥብ ከፍ በማለት በ62 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
ቦሎኛ የዛሬዉን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ ነጥቡን ወደ 65 ከፍ በማድረግ በአዉሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ለመሳተፍ ያለዉን ተስፋ ያለመልማል፡፡
ኤሲ ሚላንም በአንፃሩ የዩሮፓ ሊግ ተሳትፎን ለማረጋገጥ ነጥቡ ያስፈልገዋል፡፡
ሁለቱ ክለቦች ከዚህ ቀደም 49 ጊዜ የተገናኙ ሲሆን ሚላን 31ዱን በማሸነፍ የበላይነትን ይዟል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












