ትላንት ምሽት በተደረገው ጨዋታ ሰማያዊዎቹ ከሜዳቸው ውጪ ጣፋጭ ድል አስመዝግበዋል።
ቼልሲን ባለድል ያደርጉ ጎሎችን ኒኮላ ጃክሰን ሁለት ሲያስቆጥር፣ ጄደን ሳንቾ እና ኖኒ ማድዌኬ ቀሪዎቹን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።
ከማንችስተር ዩናይትድ በውሰት ውል ለምዕራብ ለንደኑ ቡድን የሚጫወተው ሳንቾ ከበርካታ ወራት በኋላ ጎል ማስቆጠር ችሏል።

የዴር ጉደንን ብቸኛ ግብ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ይስሃቅ አለማየሁ ሙሉጌታ ከመረብ አገናኝቷል።
የ18 አመቱ ይስሃቅ በአባቱ ኢትዮጵያዊ ሲሆን በእናቱ ደግሞ ኤልሳልቫዶራዊ ነው።
ለሁለት አመታት በኔዘርላንዱ ክለብ ፌይኖርድ የውሰት ቆይታ ካደረገ በኋላ ወደ እናት ክለቡ ዴር ጉደን ተመልሶ በዘንድሮው አመት የመሰለፍ ዕድል እየተሰጠው ይገኛል።
የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ በቀጣይ ሳምንት በስታንፎርድ ብሪጅ የሚደረግ ይሆናል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












