የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔትያንሁ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ እስራኤል ካትዝ በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ ጥቃቱን የማስጠንቀቂያ ዘመቻ(warning operation) በሚልም ጠርተውታል፡፡
በሶሪያ ድሩዝ የተባሉ ጎሳዎችን ከአክራሪ ሀይሎች ለመከላከል የተደረገ ዘመቻ እንደሆነም የእስራኤል ባለስልጣናት ተናግረዋል ፡፡
በሶሪያ መንግስት እና አክራሪ ሀይሎች መካከል በደማስቆ የተቀሰቀሰውን ግጭት ለመከላከል የእስራኤል ጦር ጣልቃ መግባቱንም የዘመቻው ሀላፊ ሊዩትናንት ጀነራል ኢያል ዛሚር አስታውቀዋል፡፡ በደማስቆ ሳህናያ አካባቢ አክራሪ ሀይሎቹ ባደረሱት ጥቃት 11 ሰዎች መሞታቸውም ተዘግቧል፡፡
አሜሪካና ሩሲያ ጥቃቱን ያወገዙ ሲሆን የአውሮፓ ህብረት በበኩሉ ፤ የቀድሞው ፕሬዝዳንት በሽር አል-አሳድ ደጋፊዎች ጊዜያዊ መንግስቱን እያጠቁት ነው ሲል ድርጊቱን ኮንኖታል፡፡ ዘገባው የአር ቲ ኒውስ ነው ፡፡
በ-ቶማይ መኮንን












