።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዳግም ወደ ነጩ ቤተመንግስት የገቡበትን 100ኛ ቀን አከበሩ።
ትራምፕ ቤተሰቦቻቸውና በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው በተገኙበት በሚቺጋን የ100 ቀናት ጉዟቸውን ያከበሩት።
በነጩ ቤተመንግስት “የስኬት ንግግር” የሚል ስያሜን የተሰጠው አንድ ሰአት የተሻገረ ንግግርም አድርገዋል።
“በአሜሪካን ታሪክ ካለፉ 100 ቀናት ስኬታማው እና ታሪካዊው ነው” ሲሉ ትራምፕ በንግግራቸው የአስተዳደር ጊዜያቸውን አቆለጳጵሰዋል።
ወርቃማ ዘመን የሚል ፅሁፍን የያዘ ባነር ከጀርባቸው አድርገው ባቀረቡት ንግግር ላይ ስለ ህገወጥ ስደተኞች፣ የህግ የበላይነትን ማስፈን፣ ተመሳሳይ ፆታን ማስወገድና ስራዎቻቸውን መመለስ ፣ ታሪፍ እና ሌሎችንም ጉዳዮች ዳሰዋል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው።
በ-የአብስራ ሚሊዮን












