በቀዳሚነት ቀን 9 ሰዓት ወላይታ ዲቻ ከ ስሁል ሽረ የሚገናኙ ይሆናል።
ከኢትዮጵያ ዋንጫ ድል በኋላ የሚመለሰው ዲቻ በፕሪምየር ሊጉ በሶስት ተካታታይ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም። በሊጉ ባደረጋቸው ሁለት ያለፉ ጨዋታዎች ተሸንፈዋል።
ወላይታ ዲቻ 37 ነጥብ በመያዝ 6ተኛ ስፍራ ላይ የተቀመጠ ሲሆን ወደ አሸናፊነት መመለስ ከቻለ በጊዜያዊነት ደረጃውን የማሻሻል ዕድል አለው።
በወራጅ ቀጠናው 17ኛ ላይ የተቀመጡት ስሁል ሽረዎች ካለፉት አምስት ጨዋታዎች ድል ማድረግ አልቻሉም። ካደረጓቸው የመጨረሻ 2 ጨዋታዎች አቻ በመውጣት ነጥብ ቢያሳኩም እጅግ ደካማ የውድድር አመት እያሳለፉ ይገኛል።
በዛሬው መርሃ ግብር የጦና ንቦቹን ድል ማድረግ ከቻሉ፣16ተኛ ላይ ከተቀመጠው አዳማ ነጥባቸውን ያስተካክላሉ።
ምሽት 12 ሰዓት ሲል በወራጅ ቀጣና የተቀመጡት ወልዋሎ አዲግራት እና አዳማ ከተማ ይገናኛሉ።ባለፉት 6 ጨዋታዎች ከአሸናፊነት የራቀው አዳማ 21 ነጥብ በመሰብሰብ ከሊጉ ላለመሰናበት እየታገለ ይገኛል።
አዳማ ከሊጉ የመጨረሻ ስፍራ ከተቀመጠው ወልዋሎ የ10 ነጥብ ርቀት ያለው ሲሆን 15ተኛ ወደ ተቀመጠው አዋሳ ለመጠጋት የዛሬውን ጨዋታ የግድ ማሸነፍ ይኖርበታል። ሁለቱም ግጥሚያዎች በተያዘላቸው ሰዓት በአዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይደረጋሉ።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












