። ።። ። ። ። ። ። ።
ፓኪስታን ህንድ ከ24 እስከ 36 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ወታደራዊ ጥቃት ልትሰነዝርባት እንደምትችል አስታወቀች፡፡
ኢዝላማባድ ከኒው ደልሂ ለሚመጣ ጥቃት ሁሉ ያለምንም ማመንታት አጸፋዊ ምላሽ ልትሰጥ እንደምትችልም ዝታለች፡፡
የካሽሚሩን ጥቃት ተከትሎ ሁለቱ ኑክሌር ታጣቂ አገራት ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ከገቡ ሳምንት አልፏቸዋል፡፡
ህንድ 172 የኑክሌር አረር ጫፍ ሲኖራት ፓኪስታን 170 እንዳሏት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
የፓኪስታን የማስታወቂያ እና ብሮድካስቲንግ ሚኒስቴር ህንድ ከ24 – 36 ሰዓታት ውስጥ ባለው ጊዜ ድንበር ተሻጋሪ ጥቃት የመሰንዘር ፍላጎት እንዳላት መረጃ ደርሶኛል ብሏል፡፡
ህንድ በካሽሚር ፓሃልጋም የደረሰውን ጥቃት ምክንያት በማድረግ ጥቃት ልትሰነዝር ነው የሚል ስጋት ያለባት ፓኪስታን ቀጠናው ወደለየለት ነውጥ ይገባል በሚል አሳስባለች፡፡
አሜሪካ እና ቻይናም የራሳቸውን ፖለቲካዊ ፍላጎት በህንድ እና ፓኪስታን ላይ ለማስፈጸም አጋጣሚውን ይጠቀማሉ የሚል መረጃም ተጋርቷል፡፡
አገራቱ ከ1947 አንስቶ ሶስት ግልጽ ጦርነት ማድረጋቸው አይዘነጋም፡፡
ዘገባው የአልጀዚራ ነው፡፡
በ- ቢኒያም ካሴ












