። ። ። ። ። ። ። ። ።
የአሜሪካ እና ብሪታንያ ሀይሎች በየመን የጋራ ወታደራዊ ጥቃት ፈጸሙ ፡፡
በየመን የሁቲ ይዞታ ላይ በተወሰደው ወታደራዊ ዕርምጃ ላይ ለንደንም ተሳታፊ ሆናለች ሲል የሰንዓው ሁቲ ከሷል፡፡
የእንግዝሊዝ ሮያል አየር ሀይል በሰንዓ አቅራቢያ ሁቲ የጦር መሳሪያ በሚያመርትበት ስፍራ ላይ ጥቃት በማድረሱ ረገድ ተባብሯል የተባለ ሲሆን፣ ከፔንታጎን በኩል ግን ምንም የተባለ ነገር የለም፡፡
ከሁቲ ጋር ግንኙነት ያለው አል-ማሲራህ ቲቪ በሰንዓ፣ በኒ ማታር፣ በኒ ሃሺሽ፣ አል ሁስን እና ሃምዳን አካባቢዎች ላይ ተከታታይ ጥቃት መድረሱን ይፋ ድርጓል፡፡
በጥቃቱም ቤቶች መውደማቸው ይፋ ሆኗል፡፡
አሜሪካ የመንን በየቀኑ በሚባል ደረጃ ከመጋቢት አጋማሽ አንስቶ በአየር እና ባህር ሀይሏ መደብደቧን ቀጥላለች፡፡
ሁቲ በቀይ ባህር በኩል ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ያላቸው መርከቦች እንዳያልፉ ማድረጉን ተከትሎ ነው ዋሽንግተን ጥቃቷን ያጠናከረችው፡፡
በዚህም በአንድ ወር ከአስራ ሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ ከ800 በላይ ዒላማዎችን ፔንታጎን መምታቱን ማሳወቁ የሚታወስ ነው፡፡
አልጀዚራ እንዳስነበበው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ












