በፊት መስመር አጥቂ ሁነኛ ተጫዋች ለምስፈረም የሚፈልጉት ቀያይ ሰይጣኖቹ ትኩረታቸውን ወደ ናፖሊው አጥቂ አዙረዋል።
ኦሲመ የዘንድሮውን አመት በቱርኩ ክለብ ጋላታሳራይ በውሰት ውል እየተጫወተ ሲሆን በውድድር አመቱ መጨረሻ ወደ ጣሊያን እንደሚመለስ ታውቋል።
የተጫዋቹ እናት ክለብ ናፖሊ ናይጄሪያዊውን ኮከብ በቡድኑ ለማቆየት ስለማይፈልግ የውል ማፍረሻውን ለሚከፍል ክለብ ለመሸጥ ተዘጋጅቷል።
ማንችስተር ዩናይትድ የውል ማፍረሻውን 51 ሚሊዮን ዩሮ ለመክፈል መዘጋጀቱን ማንችስተር ኢቭኒንግ ስታንዳርግ ዘግቧል።
የኔፕልሱ ክለብ የቀያይ ሰይጣናቱን የመስመር አጥቂ አሌሃንድሮ ጋርናቾን የሚፈልግ በመሆኑም ዝውውሩ በተጫዋች ቅያሬ ሊደረግ እንደሚችልም እየተነገረ ነው።
ለጋላታሳራይ በ36 ጨዋታዎች 31 ጎሎችና 8 አሲስቶችን ማድረግ የቻለው ቪክቶር ኦሲመ በምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲም በጥብቅ የሚፈለግ ነው ተብሏል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












