::::::::::::::::::::::::::::::::::
ዳግም ወደ ስልጣን የመጡት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሶስተኛ ጊዜ በምርጫ እንደማይሳተፉ አስታወቁ፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ለሶስተኛ ጊዜ የስልጣን ዘመናቸው የማራዘም እቅድ እንዳላቸው መግለፃቻው የሚታወስ ሲሆን አሁን ህገ መንግስታዊ ወሰንን ማለፍ ከባድ ስራ ነው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡
ፕሬዝዳንቱ የስልጣን ዘመናቸውን የመጀመሪያ 100 ቀናት አስመልክቶ በሰጡት ቃለ ምልልስ ለሶስተኛ ጊዜ የስልጣን ዘመን መወዳደር እንደሚፈልጉ ፍንጭ ቢሰጡም ያንን ማድረግ በጣም የተወሳሰበ ነገር መሆኑን ማመናቸውን ነው የገለፁት፡፡
በ2028 82ኛ አመታቸውን የሚይዙት ትራምፕ ደጋፊዎቻቸው ለሶስተኛ የስልጣን ዘመን እንዲወዳደሩ በተደጋጋሚ ሲወተውቱ እንደነበር ጠቁመው በመጨረሻ ግን ከሁለተኛ የስልጣን ዘመናቸው በዘለለ በስልጣን ላይ ለመቆየት ምንም አይነት እቅድ እንደሌላቸው ገልፀዋል፡፡
ዘገባው የአርቲ ነው
በ-ሊያ ክብሮም












