:::::::::::::::::::::::::::::::::::::
የቀበሮዎቹ ታሪካዊ ተጫዋች ከበርካታ አመታት ቆይታ በኋላ እንደሚለቅ ክለቡ በማህበራዊ ገፁ አስታውቋል።
የ 38 ዓመቱ አጥቂ የክለቡ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሲሆን በ 496 ጨዋታዎች 198 ጎሎችን ከመረብ አገኛኝቷል።

እንግሊዛዊው ተጫዋች ሌስተርን በሻምፒዮን ሺፕ ይጫወት በነበረበት ከአስራ ሶስት ዓመት በፊት ነበር መቀላቀል የቻለው።
ጄሚ ቫርዲ በክለቡ በነበረው ቆይታ የፕርሚየር ሊግ ፣ ኤፌ ካፕ ፣ ኮምዪኒቲሽልድ እና የኮከብ ግብ አግቢ ሽልማትን ማሳካት ችሏል።
33ተኛ ሳምንት በተሻገረው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሌስተር ሲቲ ከሊጉ መውረዱን አረጋግጧል።
በ – አልፈሪድ ነስሮ












