NBC Ethiopia
April 24, 2025
በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የበለጸጉ የሬይ-ባን (Ray Ban) ሜታ መነጽሮች በቅርቡ በሕንድ ለተጠቃሚዎች እንደሚቀርቡ ኩባንያው አስታውቋል፡፡ ስማርት መነጽሮቹ እንግሊዘኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ስፓኒሽ እና ጣልያንኛ ቋንቋዎችን መተርጎም ከመቻላቸውም ባሻገር ተጠቃሚዎች ለሚጠይቋቸው ጥያቄ መረጃ መስጠት እና መዚቃ ለማድመጥ ያስችላሉ፡፡

መነጽሮቹ ከኩባንያው የኢንስታግራምና ሜሴንጀር መተግበሪያዎች መልዕክቶችን፣ ፎቶዎችን፣ የድምፅ እና የቪድዮ ጥሪዎችን በቀጥታ መቀበልና መላክ እንደሚያስችሉ ተዘግቧል፡፡ ኩባንያው ሜክሲኮ እና ዩናይትድ አረብ ኤምሬትን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት መነጽሮቹን በቀጣይ ተደራሽ እንደሚያደርግ የዘገበው ኢንዲያን ኤክስፕረስ ድረ-ገጽ ፡፡

Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBC Ethiopia












