April 24, 2025
ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ተመስገን ጥሩነህ በመልእክታቸው “የቻይና ሕዝብ የፖለቲካ ምክክር ጉባኤ ብሔራዊ ኮሚቴ ምክትል ሊቀ መንበር እና የቻይና የኢንዱስትሪና የንግድ ፌዴሬሽን ሊቀመንበር የተከበሩ ጋኦ ዩንሎንግ እና የልዑክ ቡድናቸው ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደኅና መጡ እላለሁ፡፡በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለውን የኢንቨስትመንት፣ የኢኮኖሚ ልማት እና የንግድ ትብብርን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከሊቀ መንበሩ ጋር ውይይት አካሂደናል፡፡የተከበሩ ጋኦ ዩንሎንግ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለችውን የልማት እንቅስቃሴ አድንቀዋል፡፡ በተለይም መዲናችን አዲስ አበባ በእጅጉ እንደተለወጠችና ባዩት ስኬታማ ሥራ መደነቃቸውንም ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ ለቻይናውያን ባለሀብቶች ምቹ መሆኗን እና በሁኔታዎች የማይቀያየር የሁለቱ ሀገራት ስትራቴጂካዊ አጋርነት በኢኮኖሚው መስክም ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተግባብተናል፡፡” ብለዋል ::

Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBC Ethiopia












