:::::::::::::::::::::::::::::::::::::
በደረጃ ሰንጠርዡ አናት እና ግርጌ የሚገኙት ኢትዮጵያ መድን ከ አዳማ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ሆኗል።
በ45 ነጥብ ሊጉን በመምራት ላይ የሚገኘው መድን ከተከታዩ ኢትዮጵያ ቡና ያለውን የ6 ነጥብ ልዩነት ለማስፋት ማሸነፍ ይኖርባቸዋል።
በአንጻሩ 21 ነጥብ በመያዝ 16ተኛ ስፍራ ላይ የተቀመጠው አዳማ በፕሪምየር ሊጉ ለመሰንበት በቀሪ ጨዋታዎች ነጥብ መሰብሰብ የግድ የለዋል።
አዳማዎች በዛሬው ጨዋታ ማሸነፍ ከቻሉ 15ተኛ ላይ ከሚገኘው ሐዋሳ እኩል 24 ነጥብ በመያዝ በግብ ክፍያ በልጠው ደረጃቸውን ማሻሻል ይችላሉ። ጨዋታው 9 ሰዓት ሲል በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታድየም ይጀመራል።
በዚሁ ስታዲየም ምሽት 12 ሰዓት ሲል ሌላኛው የመውረድ ስጋት ያለበት ድሬዳዋ ከተማ ኢትዮ ኤሌትሪክን ይገጥማል።
በደረጃ ሰንጠረዥ በ3 ነጥብ የሚለያዩት ሁለቱ ቡድኖቹ አሸናፊ የሚሆነው ቡድን ደርጃውን የሚያሻሽልበት በመሆኑ ፉክክር ያደርጉበታል ተብሎ ይጠበቃል።
26 ነጥብ በመያዝ 14ተኛ ስፍራ ላይ የሚገኘው ድሬዳዋ ከወራጅ ቀጠና በጥቂት ነጥቦች ብቻ ርቆ የተቀመጠ በመሆኑ 3 ነጥብ ማሳካት ይኖርበታል።
ኤሊትሪክ 29 ነጥብ በመያዝ 12 ስፍራ ላይ ቢቀመጥም፣ በቀሪ የሊግ ጨዋታዎች በወራጅ ስፍራ ላይ የሚገኙ ቡድኖች ነጥብ ለመሰብሰብ ፍላሚያ የሚያደርጉ በመሆኑ ፣ አስተማማኝ ስፍራ ላይ ለመቀመጥ በትኩረት ይጫወታል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












