፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በርካታ የፈረንሳይ እስር ቤቶች ምሽቱን በተኩስ ማዕበል ሲናወጡ ማምሸታቸውን የአገሪቱ ፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የፈረንሳይ የፍትህ ሚኒስትር ጀራልድ ዳርማኒን እስር ቤቶቹ ከተሽከርካሪ ቃጠሎ እስከ በቀጥተኛ የጦር መሳሪያ ተኩስ ሲናጡ አድርዋል ብለዋል ፡፡
በተለያዩ እስር ቤቶች ጥቃት የደረሰ ሲሆን በማርሴል ፣ቱሎን እና በሌሎች አራት ቦታዎች ላይ አስፈሪው ጥቃት መከፈቱን የአገሪቱ ጋዜጦች እያስነበቡ ነው፡፡
የፍትህ ሚኒስትሩ ጀራልድ ዳርማኒን ወደ ቱሎን በመጓዝ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ባለስልጣናትን እናግዛለን በማለት በኤክስ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል ፡፡
የፈረንሳይ መንግስት ከአደንዛዥ እፅ ጋር በተገናኘ ከባድ ችግር እንደገጠመው ያስታወሱት ሚኒስትሩ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ወንጀለኞችን ጫና ውስጥ አስገብቷቸዋል ብለዋል ፡፡
ምሽቱን በተፈጠረው ቀውስ እና ጥቃት የፈረንሳይ መንግስት ማዘኑን እና ጉዳዩ እንዳሳሰበውም ተጠቁሟል ፡፡
መንግስት የእስር ቤት ሰራተኞችን ለመጠበቅ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድም ጥሪ ቀርቦለታል፡፡
ጥቃቱ ከፀረ-አደንዛዥ እፅ እርምጃ አወሳሰድ ጋር ትስስር ሊኖረው እንደሚችልም ተነግሯል ፡፡
ዘገባው የቢቢሲ እና ዶቸ ቨለ ነው፡፡
በ-የአብስራ ሚሊዮን












