::::::::::::::::::::::::::::::::::
በመድረኩ እንደ ክስተት ብቅ ያለው የእንግሊዙ አስቶን ቪላ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ፓሪስ ሴንት ዥርመንን ምሽት 4 ሰዓት ሲል ይገጥማል።
በፓርክ ደ ፕሪንስ በሚደረገው ወሳኝ ጨዋታ በአስቶን ቪላ በኩል አሰልጣኝ ኡናይ ኢምሬ እና አማካኙ ማርኮ አሴንሲዮ የቀድሞ ክለባቸውን ይገጥማሉ።
አሴንሲዮ በጥር ወር የዝውውር መስኮት በውሰት ቪላን ቢቀላቀልም ሁለቱ ክለቦች በገቡት ስምምነት መሰረት እናት ክለቡን መግጠም ይችላል።
አስቶን ቪላ እና ፒኤስዤ በወቅታዊ አቋማቸው ድንቅ የተባለ ጉዞ ላይ ይገኛሉ፣ በዚሁ መድረክ እና በየሊጎቻቸው ካደረጓቸው ያለፉት 5 ጨዋታዎች 5ቱን ድል ማድረግ ችለዋል።
ፓሪስ ሴንት ዥርመን የዘንድሮን የውድድር አመት ቻምፒዮንስ ሊጉን ያሸንፋሉ በሚል ቅድሚያ ከተሰጣቸው ቡድኖች ውስጥ ይገኛል።
በፈረንጆቹ 1982 የቻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው አስቶን ቪላ፣ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን ለማሳካት የሚፋለመውን ፒኤስዤን ይፈትናል ተብሎ ይጠበቃል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












