:::::::::::::::::::::::::::::
በደረጃ ሰንጠረዥ በ 64 ነጥብ ሁለተኛ ስፍራ ላይ የሚገኘው ናፖሊ ከመሪው ኢንተር ሚላን ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 1 ለማጥበብ ጨዋታውን ማሸነፍ ይኖርበታል።
በዋንጫ ፉክክር እስከ 31ኛ ሳምንት የደረሰው የጣሊያን ሴሪ ኤ፣ በደረጃ ሰንጠረዥ ከ 1ኛ እስከ 6ተኛ ስፍራ የሚገኙ ቡድኖች በጥቂት ነጥቦች የተራራቁ በመሆናቸው አጓጊ ሆኗል።
በ 4ተኛ ስፍራ ላይ የሚገኘው የዛሬው የናፖሊ ተጋጣሚ ቦሎኛ በሂሳባዊ ስሌት በዋንጫ ፉክክር ውስጥ በመሆኑ የምሽቱን ጨዋታ ተጠባቂ ያደርገዋል።
ቦሎኛ ባለፉት አምስት ጨዋታዎች አምስቱንም ማሸነፍ የቻለ ሲሆን በወቅታዊ አቋም ከኔፕልሱ ቡድን የተሻለ ነው።
ካለፉት አምስት ጨዋታዎች ሁለት ድል ብቻ ያስመዘገቡት ናፖሊዎች ከሚዳቸው ውጪ እንደመጫወታቸው ፈተና የሚጠብቃቸው ይሆናል። ምሽት 3፡45 ሲል በስታዲዮ ሬናቶ ዳላራ ጨዋታው ይጀምራል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












