።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እስራኤል በሶሪያ መዲና ደማስቆና ሀማ ላይ የአየር ጥቃት መሰንዘሯ ተነግሯል።
በጥቃቱ ወታደራዊ ሰፈሮችና በርካታ መሰረተ ልማቶች መውደማቸው ነው የተነገረው።
የሶሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በጥቃቱ የሀማን ወታደራዊ አየር ማረፊያ ሙሉ ለሙሉ የወደመ ሲሆን በርካታ ንፁሀን ለሞትና ለጉዳት ተዳርገዋል።
እስራኤል በሶሪያ የበሽር አላሳድ አገዛዝ ከተገረሰሰ ወዲህ እንኳ የአሁኑን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአየር ጥቃት ፈፅማለች።
ዘገባው የሮይተርስ ነው።
በ-የአብስራ ሚሊዮን












