።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሐዋሳ ላይ በሚደረጉት ጨዋታዎች ቀን 9 ሰዓት ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሃዲያ ሆሳዕና የተገናኙበት መርሃ ግብር ተጠባቂ ሆኗል።
በሊጉ በደረጃ ሰንጠረዥ 5ተኛ እና 6ተኛ ላይ የሚገኙት ቡድኖቹ የ2 ነጥብ ልዩነት ብቻ ነው ያላቸው። በ32 ነጥብ 5ተኛ ስፍራ ላይ የሚገኘው ሃዲያ ድል ማድረግ ከቻለ ባህርዳር እስኪጫወት ድረስ ሁለተኛ ስፍራን ይረከባል።
ቅዱስ ጊዮርጊስም በተመሳሳይ የደረጃ ለውጥ የሚያስገኝለት ጨዋታ እንደመሆኑ ብርቱ ፉክክር ያደርጉበታል ተብሎ ይጠበቃል።
አመሻሽ 12 ሰዓት ላይ በደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ የሚገኙት አዳማ ከተማ ከስሑል ሽረ ከሊጉ ላለመውረድ የሚያደርጉት ጨዋታም ተጠባቂ ነው።
በ20 ነጥብ 16ተኛ ስፍራ ላይ የሚገኘው አዳማ የዛሬውን ጨዋታ ካሸነፈ በጊዜያዊነት ከወራጅ ቀጠና መውጣት ይችላል።
በአንጻሩ ስሑል ሽረ በ15 ነጥብ ይዞ 17 ላይ እንደመገኘቱ ከሊጉ ላለመሰናበት ማሸነፍ ይኖርበታል።












