።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) እና ሌሎች የፌዴራል መንግሥት መሪዎች ባሕር ዳር ገብተዋል።
መሪዎች ባሕር ዳር ከተማ ሲደርሱ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ መሪዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
መሪዎች በቆይታቸው እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ይመለከታሉ። እንደ ክልል በሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ዙሪያም ከክልሉ መሪዎች ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል። ዘገባው የአሚኮ ነው።