፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ በሁለቱ አገራት ፖለቲካዊ ግንኙነት ዙሪያ መከሩ፡፡
በሞስኮ እና በቤይጂንግ መካከል ስላለው ግንኙነት እንዲሁም በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት አሁናዊ ሁኔታ ላይም ተነጋግረዋል፡፡
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ“ቻይና እና ሩሲያ የሁል ጊዜም ወዳጆች ናችው ፡መቼውኑም ጠላት የማይሆኑ ” ሲሉ ግንኙነቱን አሞካሽተውታል፡፡
ዋንግ ይ ከፑቲን በተጨማሪ ከሩሲያው አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ ጋርም ተወያይተዋል፡፡
በዋሽንግተን እና በሞስኮ መካከል ተፈጠሮ የነበረው ውጥረት እየቀነሰ መምጣቱንም በበጎ ተመልክተውታል ሚኒስትሩ፡፡
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በስትራቴጂክ ትብብር ዙሪያ የፖለቲካ ስራ ለመከወን በሞስኮ የሶስት ቀናት ጉብኝት ላይ ናቸው፡፡
ሞስኮ እና ቤይጂንግ ገደብ የለሽ ትብብር እንዳለቸውም ይታወቃል።
የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ እና የሩሲያው ፑቲን በዓለም ፖለቲካ ላይ አንድ ላይ ከመስራታቸውም ባሻገር ላለፉት አስርት ዓመታት ከ40 ጊዜ በላይ ተገናኝተዋል።
ይህም የአገራቱን የጠበቀ ወዳጅነት ያሳያል ሲል የዘገበው አልጀዚራ ነው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ












