በስድስት ነጥብ ከመሪው ባየርን ሙኒክ የራቀው ሊቨርኩሰን በሊጉ ግርጌ 16 ተኛ ላይ የሚገኘው ቦክሃም ይፈትነዋል ተብሎ አይጠበቅም። በጨዋታው ባየር ሊቨርኩሰን ወሳኝ ተጫዋቹን ፍሎሪያን ቪትዝን በጉዳት እንደሚያጣ ተነግሯል። ጨዋታው ምሽት 4፡30 ሲል በባየር አሬና ስታዲየም ይደረጋል።
ቡንደስሊጋውን በ6 ነጥብ ልዩነት እየመራ የሚገኘው ባየርን ሙኒክ ነገ ቀን 11፡30 ሲል 15ተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ሴንት ፓውሊን በሜዳው ያስተናግዳል። በቡንደስ ሊጋው ወጥነት ያለው አቋም ላይ የሚገኘው ባየርን በሜዳው ባደረጋቸው 11 ያለፉ ጨዋታዎች ሽንፈት የገጠመው በአንዱ ብቻ ሲሆን በ9ኙ ድል አድርጓል። ይህንን ተከትሎ በነገውም ጨዋታ የማሸነፍ እድል ተሰጥቷቸዋል።
ሆልስቲን ከ ወርደር ብሬመን፣ሞንቼ ግላድባህ ከአር ቢ ላይብ ዚሽ፣ቮልፍስበርግ ከ አይደን ሃየም ሌሎች በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረጉ የቡንደስ ሊጋ ጨዋታዎች ናቸው።