:::::::::::::::::::::::::::::::::::
ምሽት 4፡45 ሲል ወደ ቻምፒዮንስ ሊግ ስፍራ ለመመለስ ፉክክር ውስጥ የሚገኘው ሊዮን ከሜዳ ውጪ ከስትራስቡርግ የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል። አምስተኛ ስፍራ ላይ የሚገኘው ሊዮን ስትራስቡርግን በሁለት ነጥብ ብቻ የሚበልጥ በመሆኑ ከፍተኛ ፍልሚያ ያደርጉበታል ተብሏል።
ሊጉን በአስተማማኝ የነጥብ ርቀት በመምራት ላይ የሚገኘው ፒ ኤስ ጂ ነገ ምሽት 3ሰዓት ከሜዳው ውጪ ሴንት ኢቴይንን ይገጥማል። የፒ ኤስ ሃያልነት ሊጉን ፉክክር አልባ በማድረጉ ክለቡ ሙሉ ትኩረቱን በቻምፒዮንስ ሊግ እንዲያደርግ ሆኗል።
ለቻምፒዮንስ ሊግ ስፍራ በሚደረጉ ፉክክሮች ሞናኮ ከ ኒስ፣ ሬምስ ከ ማርሴ የሚያደርጉት ጨዋታ ሌሎች ተጠባቂ የሳምንቱ መጨረሻ መርሃ ግብሮች ናቸው።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












