።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የ19 አመቱ የአያክስ ተከላካይ ከአምናው የክረምት የዝውውር ወቅት አንስቶ ከበርካታ የአውሮፓ ክለቦች ጋር ስሙ መያያዙ ይታወሳል።
ሊቨርፑል በተከላካይ መስመሩ የቨርጅል ቫንዳይክ የረጅም ጊዜ ተተኪ ለማድረግ ካቀዳቸው ተከላካዮች መሃል ሃቶ እንደሚገኝበት ታውቋል።
ምንም እንኳን አርሰናል በተከላካይ መስመሩ አስተማማኝ ቢሆንም አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የተጫዋቹ አድናቂ መሆኑ መድፈኞቹ በፉክክሩ እንዲገቡ አድርጓቸዋል።
ኔዘርላንዳዊው ተስፈኛ በግራ መስመር እና በመሃል ተካላካይነት መጫወት የሚችል ሲሆን ለአያክስ ዋናው ቡድን እስካሁን 63 ጨዋታ ማድረግ ችሏል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ











