፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ጥምር ባለቤቶች ቶድ ቦህሊ እና ቤህዳድ ኤክባሊ አዲስ ስታዲየም በማስገንባቱ የተለያዩ አቋም ላይ ቢገኙም ሃሳቡ በቦርድ አባላቱ ተቀባይነት አግኝቷል።
እ.አ.አ በ1905 የተገነባው 40ሺ ተመልካቾችን የማስተናገድ አቅም ያለው ስታምፎርድ ብሪጅን ለማስፋፋት ሃሳብ የነበረ ቢሆንም ሜዳው የሚገኝበት አካባቢ አመቺ አለመሆኑ ታውቋል።

ስታምፎርድ ብሪጅን በማፍረስ በርካታ ተመልካቾችን ማስተናገድ የሚችል አዲስ ስታዲየም መገንባት የ ቶድ ቦህሊ እቅድ መሆኑ ታውቋል።
በሌሎች ክለቦች እየታየ እንዳለው የስታዲየም ገቢን በማሳደግ እና የስያሜ ሽያጭ በማድረግ የክለቡን ፋይናንስ ለማጠናከር ወጥነዋል።
ቼልሲ በጊዜያዊነት ዌንብሌን ለመከራየት እንዳቀደ የተነገረ ሲሆን አዲሱን ፕሮጀክት መች ለመጀመር እንደታቀደ ግን አልተነገረም።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












