::::::::::::::::::::::::::::::
የሪያል ሶሴዳዱ አማካኝ በጥር ወር የተጫዋቾች የዝውውር ገበያ በክረምቱ ወደ ሰሜን ለንደኑ አርሰናል እንዲዘዋወር መድፈኞቹ ከክለቡ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው አይዘነጋም።
ይሁን እንጂ ተጫዋቹ ባሳለፍነው ክረምትም ወደ መርሲሳይዱ ሊቭርፑል ሊጓዝ ተቃርቦ ሃሳቡን በመለወጥ በሶሴዳድ መቆየትን መርጧል።
ምንም እንኳን መድፈኞቹ ከባስኩ ክለብ በዝውውር ጉዳዮች የሰመረ ግንኙነት ቢኖረውም ሪያል ማድሪድ የተጫዋቹን ሃሳብ ሊያስቀይረው እንደሚችል ተገምቷል።
በክረምት አማካኝ መስመር ተጫዋቾቹን ቶማስ ፓርቴን እና ጆርጊኒሆን ይለቃል ተብሎ የሚጠበቀው አርሰናል የ26 አመቱን ስፔናዊ አማካኝ ወደ ክለቡ የማምጣት ጥረቱ ፈተና ገጥሞታል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












