Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ለፊቼ-ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ:::::::::::::::::::::::::::::::::

March 27, 2025
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

ሲዳማ የስነ ከዋክብት ዑደትን በማጥናትና በመመርመር የወቅቶችን እርዝማኔና ንባሬ በማጥናት ሽርፍራፊ ሰከንዶችን ፥ደቂቃዎችንና ሰዓታትን ቀምረው ቀናትን፥ሳምንታትን ፥ወራትንና አመታትን የሚለኩበት የቀደምት እውቀት ጥግ ማሳያ ለሆነው ፊቼ-ጫምባላላ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!

የሲዳማ ህዝብ በርካታ ባህሎችና ትውፊቶች ባለቤት ስሆን ከነዚህም ውስጥ አንዱ የዘመን መለወጫ ፊቼ-ጫምባባላ በዓል አንዱ ነው።

ህዝቡ የቀደምት እውቀት ጥግ ማሳያ የሆነው ፊቼ-ጫምባላላ በዓል ለህዝባችን የጥበብ ጥግ፣ ለሀገራችን ኩራት እና ለአለማችን እንቁ ባህላዊ ቅርስ ነው።

ፊቼ- ጫምባላላ በሲዳማ ብሔር የአዲስ ዓመት ዘመን መለወጫ በዓል ሆኖ የሚከበር ሲሆን በብሔሩ ተወላጆች ዘንድ ለብዙ ሺ ዓመታት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሸጋገር የመጣ ባህላዊ ትውፊት ነው።

ሲዳማ የራሱ የሆነ ጊዜን፥ወቅትንና ዘመንን የሚቀምርበት ባህላዊ እውቀትና ጥበብ ያለው ህዝብ ሲሆን ይህን ባህላዊ እውቀቱንና ጥበቡን ከትውልድ ወደ ትውልድ እያሸጋገረ ለዚህ ትውልድ አድርሶታል።

የሲዳማ አባቶች (አያንቶዎች)ባህላዊ የስነ ፈለክ (Astronomy )ምርምር እውቀትና ጥበባቸው የረቀቀ ሲሆን የሰማይ ከዋክብትን የፀሐይንና የጨረቃን ህብራዊ ውህደትንና ተናጠላዊ አንድምታን በመመርመር የወቅቶችን እርዝማኔና ንባሬ በማጥናት ሽርፍራፊ ሰከንዶችን ፥ደቂቃዎችንና ሰዓታትን ቀምረው ቀናትን፥ሳምንታትን ፥ወራትንና አመትን የሚለኩበት የሲዳማን የቀን አቆጣጠር ካላንደር የፈጠሩ ናቸው።

ያኔ ዓለማችን በዘመናዊ የሳይንስ ፥እውቀትና ቴክኖሎጂ ባልረቀቀበት ዘመን፤ አብዛኛውን የአለማችን ህዝቦች ንቃተ ኅሊናቸው ባላደገበት ዘመን ፤ በጥንታዊ ኋለቀር የአኗኗር ስርዓት ዘመን ቀደምት የሲዳማ አባቶች /አያንቶዎች/የሰማይን ተፈጥሮዋዊ ምንነት፥የምድርን አቀማመጥ፣የከዋክብትንና የጨረቃ ሥርዓትና ውሁደት መርምረውና አጥንተው ይሄው ለዛሬው ለኛ ትውልድ ይህን የቀንና የጊዜን መለኪያ ባህላዊ ጥበብ አድርሰዋል።

ይሄም የሲዳማ ባህላዊ የቀን አቆጣጠር ጥበባዊ እሴት ትንታኔ በአለም አቀፍ ቅርስነት መመዘኛዎች የሚመጥን ሆኖ በመገኘቱ ከዛሬ አስር አመት በአለም አቀፍ ቅርስነት በUNESCO በማይዳሰሱ ቅርሶች አንዱ ሆኖ ሊመዘገብ አስችሏል ፤ በተጨማሪም የአለም የጋራ ሀብት ጥበቃና እንክብካቤ ከሚደረግላቸው እና እውቅና ካገኙ አለም አቀፍ ቅርሶች አንዱ ለመሆን በቅቷል።

በሲዳማ ብሔረሰብ በፊቼ -ጫምበላላ በዓል ለተፈጥሮ እፅዋትና ስነ ምህዳር ልዩ እንክብካቤና ጥበቃ የሚደረግና የሴቶችና ህፃናት መብት የሚከበርበት ወቅት ሲሆን ለደን ፥ለአፈና ለውሃ ጥበቃ እንዲሁም ለተፈጥሮ የሚሰጠው ክብር የላቀ በመሆኑ እነዚህ ባህላዊ እሴቶች ተተንትነው ፊቼ -ጫንባላላን በአለማቀፍ ቅርስነት እንዲመዘገብ ካስቻሉት ነጥቦች የተወሰኑቱ ናቸው።

ፊቼ -ጫምባላላ ከአሮጌው አመት ወደ አዲስ ዓመት መሸጋገሪያ የዘመን መለወጫ በዓል ሲሆን በዓሉ ሲከበር ቂም፥ቁርሾና በቀል ይዞ ወደ አዲሰ ዘመን መሻገር ስለማይፈቀድ የሲዳማ ህዝብ በሁሉቃ ስርዓት ቂም ፥ቁርሾና በቀሉን በይቅርታ የሚያወርድበት በዓል ነው።

ስለዚህም የተጣላ የሚታረቅበት፤ ቂም የያዘ ቢኖር ቂሙን የሚረሳበት፤በሰዎች መካከል ይቅርታ ፥መቻቻልና አብሮነት የሚጎለብትበት ፤ፍቅርና መተሳሰብ የሚሰፍንበት በዓል በመሆኑ አሁን በሀገራችን በህዝቦች መሐል እየተከሰተ ላለው ለጥላቻና ግጭት ጉልህ ማስተማሪያ ሊሆን የሚችል ባህላዊ እሴት ነው።

በፊቼ -ጫምባላላ የሲዳማ ህዝብ ሌሎች ብሔር ብሔረሰቦችን በማቅረብ አቃፊነትፈቱን የሚያንፀባርቅበት ፤ በህብረተሰቡ መሀከል ወንድና ሴት ተብሎ የፆታ ልዪነት የማይደርግበት ፤ህፃን ፥አዋቂና አረጋዊ ተብሎ ሳይከፋፍል ሁሉም በአንድ አይን የሚታይበትና አንዲሁም ለእንስሳት ልዩ እንክብካቤ በመስጠት በዓሉ የሚከበርበት ዕለት ነው።

ፊቼ- ጫምባላላ ለሲዳማ ብሔረሰብ ተወላጅ ብቻ ሳይሆን አብሮ በሚኖረውም ማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ እንድምታ የሚሰጠው ሲሆን ህዝባዊ ፍቅር የሚገለፅበት ፤የተጣሉ የሚታረቁበት እንዲሁም የሰላምና የልምላሜ መገለጫም ጭምር ሆኖ ይቆጠራል።

ፊቼ -ጫምባላላ በብሔረሰቡ ተወላጆች ዘንድ የፍቅር ፥የሰላም ፥የአንድነት ፥ የአብሮነትና የመተሳሰብ ተምሳሌት በመሆኑ በዓሉ በአለም ቅርስነት መመዝገቡ ፋይዳው የጎላ ነው ። እንዲሁም የሲዳማን ሀገር በቀል እውቀትና የብሔሩን ባህላዊ የስነ ከዋክብት ጥናት ጠበብትነትን ለአለም ህዝብ የተዋወቀበት ስለሆነ ለቱሪዝም ኢንዱስትሪያችን መበልፀግ የራሱን አስተዋፅኦ ያበረክታል ።

መንግሥታችን ለባህላዊ ጥበቦችና እውቀቶች ላቅ ያለ ትኩረት በመስጥ በትውልዱ ውስጥ የጋራ አብሮነትን ሊያጠናክሩና ሊያስተሳስሩ የሚችሉ እሴቶችን የመገንባትና የማፅናት ኃላፊነትን ወስዶ እየሰራ ያለ ሲሆን የወንድማማችነትንና የእህትማማችነትን መርህ መሠረት በማድረግ ህብረብሔራዊት ኢትዮጵያ ለመገንባት በሚያከናውነው የሰላምን ግንባታ አውድ ፊቼ ጫምባላላ የጎላ ፋይዳ ይኖረዋል።

የሲዳማ ብሔረሰብ ከአቃፊነቱ ባሻገር እጅግ ተወዳጅና ተናፋቂ የሆነውን የፊቼ- ጫምባላላ በዓል ሚያከብረው በአንድነትና በጋራ በመብላትና በመጠጣት ፤ ያለው ለሌለው በማካፈል ፤በመረዳዳትና በመተሳሰብ ሲሆን ይሔን አኩሪ የሆነ ደማቅ ባህለዊ ትውፊታችንን በማጉላት አሁንም እንደ ቀድሞው ያጡትን በመደገፍና በመርዳት ፤ የአካባቢያችንንና የቄያችንን ሰላም በመጠበቅ ከክፋትና ካተገባ ተግባር ራሳችንን አቅበን በዓሉን በደስታ እያከበር ወደ አዲሱ ዘመን እንሸጋገር እላለሁ ።

በድጋሚ እንኳን ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል በሰላም አደረሰን !

ShareTweetShare
Previous Post

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማስተር ካርድ የክፍያ ሥርዓትን አስጀመረ

Next Post

“ከአሜሪካ ጋር ያለን ግንኙነት አብቅቷል!” የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
“ከአሜሪካ ጋር ያለን ግንኙነት አብቅቷል!” የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር

"ከአሜሪካ ጋር ያለን ግንኙነት አብቅቷል!" የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር

“አውሮፓውያን አደጋ ውስጥ ናቸው ” የአውሮፓ ህብረት

"አውሮፓውያን አደጋ ውስጥ ናቸው " የአውሮፓ ህብረት

ፊቼ ጫምባላላ በሶሬሳ ጉዱማሌ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል

ፊቼ ጫምባላላ በሶሬሳ ጉዱማሌ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?