።።።።።።።።።።።።።።።።።
የፌስቡክና ኢንስታግራም እናት ድርጅት ሜታ የቀድሞ ሰራተኛው ስለ ካምፓኒው ጽፋ ያሳተመችውን መጽሐፍ እንዳታስተዋውቅ በፍርድ ቤት እንድትከለከል ማድረግ ችሏል።
“ግድየለሽ ሰዎች (Careless People)” የተባለውን መጽሐፏን ያሳተመችው የሜታ የቀድሞ የአለም አቀፍ የህዝብ ፖሊሲ ዳይሬክተር የነበረችው ሳራ ዊን-ዊሊያም ስትሆን ሜታ ለፍርድ ቤት ባቀረበው አስቸኳይ ቅሬታ ምክንያት ደራሲዋ መጽሐፉን ማስተዋወቅና ድጋሚ ማሳተም ተከልክላለች።
ኒውዮርክ ታይምስ መፅሃፉን “በአለም ላይ ካሉት ታላቅ ኩባንያዎች አንዱ ስለሆነው ሜታ እና ማርክ ዘከርበርግን ጨምሮ ስለመሪዎቹ አስቀያሚ ጎን በዝርዝር የተጻፈ” ሲል ገምግሞታል።
ጉዳዩን የተመለከተው የአሜሪካ የግልግል ዳኛ ማህበር በሰጠው ብይን መጽሐፉ ሜታ ላይ በቀላሉ የማይጠገን ኪሳራ ሊያደርስበት ይችላል ሲል ተናግሯል።
የሜታ ቃል አቀባይ አንዲ ስቶን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በለጠፈው ጽሑፍ “ይህ ውሳኔ የሳራ ዊን ዊልያምስ መጽሐፍ በውሸት እና ስም ማጥፋት የተሞላ እንደሆነና መጀመሪያውኑም በጭራሽ መታተም እንዳልነበረበት ያረጋግጣል።” ብለዋል። ዘገባው የሮይተርስ ነው።
በ-ዳንኤል መኮንን












