አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከስዊድን የፍትህ ሚኒስቴር ዋና ተጠሪ አንደርስ ሆል ጋር ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
አምባሳደር ምስጋኑ ኢትዮጵያ እና ስዊድን ስላላቸው የረጅም ጊዜ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዳላቸው አውስተዋል።
ሀገራቱ አቅምን ግንባታን ጨምሮ በፍትህ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል።
በተጨማሪም የሀገራቱን የሁለትዮሽ ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሀሳቦችን መለዋወጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።












