በስልጠና ጥራትና አቅርቦት መካከል ያለውን ክፍተት ለመድፈን በክህሎት ልማት ላይ የግሉ ዘርፍ ሚና ወሳኝ ስለመሆኑም ተመላክቷል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያዘጋጀው ሁለተኛ ምዕራፍ ሶስተኛ ዙር “ስለኢትዮጵያ” የፎቶግራፍ ዓውደርዕይና የፓናል ውይይት መካሄድ ጀምሯል።


በፎቶ ግራፍ አውደ ርዕዩ ጥንታዊ የክህሎት አጀማመር መሠረቶች፣ በሰመር ካምፕ እና በስታርት አፕ የተሰሩ ሥራዎች፣ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ተማሪዎች የተሰሩ ማሽኖች እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ የተገኙ ውጤቶች ለእይታ ቀርበዋል።
መድረኩ ”ክህሎት ስለኢትዮጵያ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ የሚካሄድ ሲሆን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር)፣የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በ- ሔርሜላ ፍቃደ












