።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አዲስ አበባ | ጥር 12 2017 | NBC ETHIOPIA -የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በአዲስ አበባ በተካሄደው የከተራና የጥምቀት በዓል ምንም ዓይነት አደጋ ሳያጋጥም ተከብሮ መጠናቀቁ ተገለፀ ።
ኮሚሽን መ/ቤቱ በዓሉ ያለአደጋ ክስተት ተከብሮ እንዲያልፍ ከሀይማኖት አባቶችና ከበዓሉ አስተባባሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ ሚዲያዎች ጋር በመሆን ህብተሰቡ ለአደጋ የሚያጋልጡ አሰራሮችን ተገንዝቦ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክቶችን ሲያስተላልፍ ቆይቷል።
በዚህም በዓሉ ያለምንም አደጋ ክስተት ተከብሮ ማለፉን ነው ከኮሚሽን ማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ከኮሚሽን መስሪያ ቤቱ የተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ በማድረግና የጥንቃቄ መልዕክቶች በማስተላለፍ ህብረተሰቡና የሚዲያ አካላት ላደረጉት አስተዋጽኦ ኮሚሽኑ ምስጋና አቅርቧል።
በበዓላት ጊዜ የተደረጉ የጥንቃቄ ተግባሮች በመደበኛና በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችም ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው ኮሚሽኑ አሳስቧል።












